መጋቢት 11/2016 ዓ.ም በቦሎሶ ሶሬ ወረዳ በዳንጋራ ሳላጣ ማዘጋጃ የማርጯ አነስተኛ የፋይናንስ ተቋም አ.ማ የአረካ እና ቦሎሶ ሶሬ ወረዳ ቅርንጫፍ በዛሬ ዕለት የሥራ ንቅናቄ መድረክ አካሂደዋል።
ማርጯ አነስተኛ የፋይናንስ ተቋም የህዝቡን ፍላጎት በማሟላት የኢኮኖሚና የሀብት ጥንካሬ እንድኖር ለማድረግና የገንዘብና የሀብት አቅም ከፍ ለማድረግ ታልሞ የተቋቋመ ተቋም እንደሆነ ተገልፆዋል።
ማርጯ አነስተኛ የፋይናንስ ተቋም የሚሰጣቸው አገልግሎቶች የግል ብድር ፣ አነስተኛ ንግድ ብድር ፣ኢንተርፕራይዞች ብድር ፣ የተቀጣሪ ሰራተኞች ብድር ፣ የግብርና ምርት ንግድ ብድርና የማህበራት ብድር እንደሚሰጥ ተገልጸዋል።
ማርጯ አነስተኛ ፋይናንስ ተቋም የእኔ ነው በማለት ከተለያዩ ዕድር አባላት ጀምሮ ያሉ የገንዘብ ቁጠባ ማህበራት ወደ ማርጯ አነስተኛ ተቋም በማምጣት በመቆጠብ መጠቀም እንደሚገባም ተጠቁመዋል።
ሁሉም ህብረተሰብ ክፍል በማርጯ አነስተኛ የፋይናንስ ተቋም በመቆጠበና ቁጠባን ባህል በማድረግ እንድጠቀሙ ጥሪ ተደርገዋል።
በመጨረሻም የዳንጋራ ሳላጣ ማዘጋጃና አከባቢ ነዋሪዎች ማርጯ አነስተኛ የፋይናንስ ተቋም አክስዮን ማህበር የየራሱን የቁጠባ ደብተር በመክፈት ቁጠባ መጀመራቸውና አጠቃላይ ህብረተሰብ ክፍል እንድቆጥብ ለማድረግም መስማማታቸው ተገልጿል።
ዘወትር ቆጥቡ፣ለቁም ነገር ተበደሩ፣ በጊዜው ክፈሉ!