ወላይታ ሶዶ ሚያዝያ 16/2016 ዓ.ም በወላይታ ዞን ጉኑኖ ሐሙስ ቅርንጫፍ ማርጯ አነስተኛ የፋይናንስ ተቋም አ.ማ የሥራ ማስጀመሪያ መድረክ አካሄድ።
የፋይናንስ ተቋሙ ከብሔራዊ ባንክ ሙሉ የሥራ ፈቃድ አግኝቶ አስፈላጊውን ስራ እየሰራ መቆየቱን ተገልጿል።
የህዝቡን ኢኮኖሚያዊ ጠቀሜታ ለማረጋገጥ የጥንት የወላይታ ህዝብ መገበያያ ገንዘብ በሆነው “ማርጯ” በመሰየም ማርጯ አነሰተኛ ማይክሮ ፋይናንስ ተቋምን በመመስረት ሙሉ ስራውን ጨርሶ ወደ ተግባር መግባት መቻሉ ተጠቅሷል።
ማስጀመሪያ መድረክ እየተካሄደ ሲሆን የወላይታ ዞን አስተዳደር ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ጻድቁ ፈለቀ፣ የማርጯ ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ አበበ ሳዮሬ፣ የወልማ ስራአስኪያጅ አቶ አሰፋ ናና፣ ጨምሮ የከተማና ወረዳ አስተዳዳሪዎች፣ የመንግስት ዋና ተጠሪዎችና ሌሎች የፋይናንስ ተቋም አባላት ተሳትፈዋል።